ማሻ፣ ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) “ሀሳብ የለውጥ ኃይል ነው። ምሁራን ደግሞ የለውጥ ወኪሎች ናቸው። ምሁራን በማኀበረሰብ ውስጥ የሚፈጥሩት ለውጥም ሀገርን ወደ ብልጽግና ይወስዳል። በመሆኑም ምሁራን ሀሳብ አክባሪና አፍቃሪ፣ ጥልቅ አሰላሳይ፣ አንባቢ፣ ችግር ፈቺና መፍትሄ አሳሽ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማስመልከት ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ጽሁፍ በማቅረብ ተሳትፍያለው። በመድረኩም የኢትዮጵያ ምሁራን በሁለንተናዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሚና በሚመለከት ሰፊ ውይይት አድርገናል።
የመደመር መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ ላይ አይተኬ ሚና እንዳላቸው በጽኑ ያምናል፣ ለተግባራዊነቱም እየሰራ ይገኛል።
ተቋማቱም የመማር ማስተማር እንዲሁም የምርምር ስራዎችን ከቴክኖሎጂ ጋር በማናበብ ወደ ፈጠራና ተግባር መለወጥ ይጠበቅባቸዋል። ይህም የኢትዮጵያን ብልጽግና በተደመረ አቅም ለማፋጠን ሚናው ከፍተኛ ነው።”
፨ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች