ማሻ ፣ የሀምሌ 07፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምክር ቤቱ የክልሉን አስፈፃሚ አካላት ተግባር በየደረጃው በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።
አክለውም የመድረኩን አላማ በማስረዳት፣ የአፈፃፀም ሪፖርቱ የምክር ቤቱን ደንብ በጠበቀ መልኩ እንዲቀርብ አሳስበው መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል።
በዚህም መሰረት ህግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር፣ ግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች፣ በጀትና ፋይናንስ፣ ከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች በየዘርፉ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
መድረኩ ለተከታታይ 2 ቀናት እንደሚካሄድ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በመድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፀሀይ ደርጫን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ አመራሮችና የየዘርፉ ባለሙያዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ የደቡብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።
ክልል ኮሚኒኬሽን
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች