ማሻ ፣ የሰኔ 30፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በመርሃ ግብሩ የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች እና የሚዲያ አካላት ተሳትፈዋል።
እንደ ሀገር ጽዱ ኢትዮጵያ ፣ጽዱ አካባቢ መረሃ ግብር ተቀርጾ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ሰነባብቷል ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም ይህ ኢኒሼቲቭ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ እየተከናወነ ይገኛል።
የዚሁ አካል የሆነው አካባቢን የማጽዳት ስራዎችን በማከናወን ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በዞኑ ቴፒ ከተማ አስተዳደር ህብረት ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በማለዳ ወጥተው አጽድተዋል።
በአካባቢ ጽዳት የተሳተፉ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት ከቤት ጀምረው አካባቢያቸውን በጋራ የማጽዳት ስራዎችን አጠናክረው እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል ።
በዚህም በአከባቢው የወባ በሽታ ስርጭት ከባለፈው ወዲህ በእጅጉ እየቀነሰ መምጣቱንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል ።
የቴፒ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዋሲሁን አውሎ በሰጡት አስተያየት በከተማው ባሉ 3 ቀበሌዎች የአካባቢ ጽዳት ስራ ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
በየሳምንቱ ህዝቡ ወጥቶ አካባቢውን በማጽዳቱ የወባ በሽታ ስርጭት እየቀነሰ መምጣቱንም አቶ ዋሲሁን ተናግረዋል ።
ህብረተሰቡ የጀመረውን የአካባቢ ጽዳት ስራ የበለጠ በማጠናከር አካባቢውን ጽዱ ማድረግ እንደሚገባቸውም አቶ ዋሲሁን ተናግረዋል ።
በጽዳት ስራው የቀበሌው ነዋሪዎች ፣የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና የሚዲያ አካላት ተሳትፈዋል።
ክልል ኮሚኒኬሽን
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች