የመዲናዋ የልማት ሥራ ለሌሎች አፍሪካ ከተሞች አርአያ የሚሆን ነው – የተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች
ማሻ ፣ የሰኔ 14፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም)በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘው የልማት ሥራ በሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው አሉ የአፍሪካ የሕጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎቸ፡፡
የተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች የተካተቱበት የአፍሪካ የሕጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ልዑካን በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው ሁሉን አቀፍ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ልማት ከተማዋን ጽዱ እና ለኑሮ ምቹ የሚያደርግ ነው፡፡
የኮሪደር ልማቱ እና ሌሎች የልማት ሥራዎች የአዲስ አበባን የአፍሪካ መዲናነት የሚመጥኑ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡
በአዲስ አበባ አሁን ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ አካታች የልማት ሥራዎች ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች አርአያ አንደሚሆኑ አጽንኦት መስጠታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
በተለይም ለሕጻናት እና ታዳጊ ወጣቶች የተከናወኑ ሥራዎች፣ ከተማዋን ጽዱ ለማድረግ የተገነቡ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ ለአረንጓዴ ስፍራና ለወንዝ ዳርቻ ልማት የተሰጠው ትኩረት የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ለቅርስ ጥበቃ የታሪክና የማንነት ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለትውልድ ለማስተላለፍ የተሰራው ሥራ የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የልማት ሥራው የሕዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ በመሆኑ ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች በከተማ ልማት ረገድ ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን አመልክተዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ መረጃ ያመለክታል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች