ማሻ ፣ የሰኔ 07፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም)ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የመምህራን ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ የመምህራን ጥያቄዎች ሌሎችንም አካታች በሆነ ማዕቀፍ ሊታዩ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የመጀመሪያው ሀገር ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን እንዳለበት ጠቅሰው፤ ከዚያ ውጭ የሚቀርበው ንጽጽር ግን ኢትዮጵያ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር ስለማይሄድ ዋጋ የለውም ብለዋል።
ነጻ ሕክምና፣ ነጻ ትምህርት፣ መኖሪያ ቤት የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሲጠየቁ የወታደሩን፣ የሐኪሙን እና የሌላውንም ደምሮ ማየት እንደሚያስፈልገ አመላክተዋል።
“እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው፣ መኪናቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤታቸው በር ላይ አቁመው ሲያስተምሩ ከማየት በላይ ለኔ ደስታ የለም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ውስጥ ውስጡን እየተሠሩ ያሉት ሥራዎች ሲሳኩ የመምህራን ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል።
የመምህራን ጥያቄ በደመወዝ ጭማሪ ብቻ የማይመለስ መሆኑን አንስተው፣ የደመወዝ ጭማሪው ላይ ብቻ ትኩረት ከተደረገ ያለችው ተበልታ ታልቃለች በማለት የሚከተለውን መዛባት ጠቁመዋል።
ያለችውን በልቶ ከመጨረስ በራስ ላይ ጨክኖ ገበታን ማስፋት፤ ለዚህ ደግሞ ምርትን ማብዛት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።
የመምህራን ጥያቄ ከሌሎች ጥያቄዎች ጋር ታይቶ ነገን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መመለስ እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ኢቢሲ
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች