ማሻ ፣ የግንቦት 13፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በሸካ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ባለድርሻ አካላት “የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በማሻ ከተማ ውይይት አካሂዶዋል ።
በሀገራችን ባለፋት የለውጥ ዓመታት በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች በሚደያና ኮምኒኬሽን በማስተዋወቅ መላው ህዝብ የልማት ተነሳሽነቱን እንዲያሳድግ መስራት እንደሚገባ በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ጠቁሟል።
በዞኑ የተቋቋመው ሚዲያ አንዱ የለውጥ አካል መሆኑን ገልፀው እውነተኛና ሚዛናዊነት የጠበቀ መረጃ በማሰራጨት እንዲሁም እንደ ሀገር ታሪካዊ ገድሎችን፣ መልካም ባህላዊ እሴቶቻችን እንዲሁም የቱሪስት መስህቦችንና ፀጋዎችን በማስተዋወቅ ለሃገር ገጽታ ግንባታ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ለውይይቱ ተሳታፊዎች አሁን ለምንገኝበት ዓለምአቀፋዊ እና ሀገራዊ ሁኔታ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ባቀረቡት ሪፖርት የገለፁት የሸካ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙልጌታ አድራሮ በሚከሰቱ ሁኔታዎች የማይናወጥ ጠንካራ ሚዲያ በመፍጠር ውጤታማ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከል ላይ ትኩረት ልደረግ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ከነጠላ ትርክት ወጥተን ገዥ ትርክትን መገንባት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሙልጌታ የለውጡ መንግስት ለሚዲያ ነጻነት ፈር ቀዳጅ ስራ የሰራ ቢሆንም ይህንን ነጻነት ለመልካም ስራ የተጠቀሙት የሚዲያ አካላት እንዳሉ ሁሉ ባልተገባ መንገድ ለጥፋት የሚጠቀሙ አካላትን መከላከል እንደሚገባም ተመልክቷል።
የቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግ የመድረኩ ተሳታፊዎች ቀጣይ በዘርፉ የተሻለ ለውጥ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ ሀሳቦችን አንስተዋል ።
ሚዲያ ዘላቂ ሰላም፣ አንድነትና ብልጽግናን በማረጋገጥ ረገድ እምቅ አቅም ያለው ተቋም በመሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች በማሰራጨት ለሁለንተናዊ ልማትና እድገት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለባቸውም የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ጠቁመዋል ።
የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ለግል ጥቅማቸው የሚንቀሳቀሱ፣ ከውጭና ከውስጥ የሀገራችንን ለውጥ የማይፈልጉ አካላት እንዲሁም የእርስ በእርስ ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩትን በጋራ ለመከላከልና ውጤታማ ለውጥ በሀገራቱ እንዲመዘገብ ከማድረግ አንፃር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሰዋል።
በዞኑ “ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት ተጠናቀው አገልግሎ በመስጠት ላይ የሚገኘውን ማሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና የማሻ ሳብስተሺን ያለበትን ደረጃ ጉብኝት በማድረግ ውይይቱን አጠናቋል።
ዘጋቢ ወንድማገኝ ገሪቶ
More Stories
አፍሪካ በሀገር በቀል አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል
ቲክቶክ በአውሮፓ ክስ ቀረበበት