May 20, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጆ ባይደን በካንሰር ህመም መያዛቸው ተነገረ

ማሻ ፣ የግንቦት 11፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ‎‎የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በካንሰር ህመም መጠቃታቸውን ጽ/ቤታቸው አስታውቋል።

የ82 አመቱ ጆ ባይደን በከባድ የፕሮስቴት ካንሰር መጠቃታቸውና በካንሰር የተጠቃው ህዋሳቸው ወደ አጥንታቸው መዛመቱ ተነግሯል።

የፕሬዚዳንቱ የካንሰር ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ በሚደረግላቸው የህክምና አማራጮች ዙሪያ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እየመከሩ ነው ሲል አሶሺየትድ ፕረስ ዘግቧል።

የወቅቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጆ ባይደን ባስተላለፉት መልዕክት፥ በሁኔታው ማዘናቸውን ገልጸው ከህመማቸው በፍጥነት እንዲያገግሙ ተመኝተዋል።

ፋና