ማሻ ፣ የግንቦት 08፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያው ቲክቶክ የአውሮፓ ህብረትን የዲጂታል አገልግሎት ሕግ ጥሷል በሚል ክስ ቀርቦበታል።
በዚህ ክስ የቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ ከዓለም አቀፍ ገቢው እስከ 6 በመቶ የሚደርስ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት ሥራ አስፈፃሚ፥ ቲክቶክ ተጠቃሚዎቹ የማጭበርበሪያ ማስታወቂያዎችን ለይተው እንዲያውቁ የሚያስችላቸውን የዲጂታል አገልግሎት ሕግ ማክበር አልቻለም ብሏል።
በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ቲክቶክ ለማስታወቂያ ለማን እንደሚከፍል፣ ማስታወቂያው ማን ላይ እንደሚያነጣጥር እና ማስታወቂያዎቹ ምን እንደያዙ በግልፅ እያሳየ አለመሆኑን ገልጿል።
በሌላ በኩል ክስ የቀረበበት ቲክቶክ የአውሮፓ ህብረት የዲጂታል አገልግሎት ሕግን የተረዳበትን መንገድ አልደግፍም ሲል ተቃውሟል።
ቲክቶክ መተግበሪያውን ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ግልፅ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል::
የማስታወቂያ አሠራሩን ለሕዝብ ክፍት ለማድረግም በንቃት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ኢቢሲ
More Stories
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል
የዜጎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በነጻ የቀረበው የኮደርስ ስልጠና
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ“ቴክ ቶክ ከሰለሞን ጋር” በክፍል አንድ በነበራቸው ቆይታ ካነሷቸው በርካታ ጉዳዮች መካከል፡-