ማሻ ፣ የግንቦት 05፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥሉት አራት ቀናት የሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ የሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸውን የመጀመሪያ የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸውን በሳዑዲ አረቢያ ጀምረዋል።
ዛሬ ሪያድ የገቡት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሀገሪቱ መሪ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ዋነኛ ዓላማ ለአሜሪካ ኢኮኖሚ ትልቅ አዲስ ኢንቨስትመንትን ለማስፈን ያለመ ስለመሆኑ ተዘግቧል፡፡
በሳውዲ አረቢያ ቆይታቸው የሳውዲ-አሜሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የሚሳተፉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፤ ጉብኝታቸው በመጪው አርብ የሚጠናቀቅ መሆኑ ተመላክቷል።
Fana
More Stories
ትራምፕ ቲክ ቶክን የሚገዙ የአሜሪካ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን ገለፁ
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ