ማሻ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ደሬተድ ማሻ ቅርንጫፍ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተረከበው ቦይንግ 737-800 የተሰኘ የቢዝነስ ጀት አውሮፕላን ልዩ አገልግሎት ለሚሹ ደንበኞቹ እንደሚውል ተጠቁሟል።
ከዚህ ቀደም ለልዩ በረራዎች የሚውሉ አገልግሎቶችን በመደበኛ አውሮፕላኖች ሲሰጥ መቆየቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
አዲሱ አውሮፕላን ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ውስጣዊ ክፍሎች እንዳሉት ገልጸው፤ በመደበኛ አገልግሎት ላይ ይፈጥር የነበረውን ጫና እንደሚቀንስ ጠቁመዋል።
አየር መንገዱ በቻርተር አውሮፕላን አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አቅሙን ለማሳደግ መሰል አውሮፕላኖች እንደሚያግዙት ተናግረዋል።
አየር መንገዱ በ2035 የአገልግሎት አድማሱን ለማስፋት የያዘውን ውጥን ለማሳካት መሰል ተጨማሪ የቢዝነስ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ እንደሚስገባ ተገልጿል።
ኤፍ ኤም ሲ
More Stories
አዲሱ የማዕድንና ኢንዱስትሪ ትስስር
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አቪዬሽን ኢንዱስትሪ የጀርባ አጥንት መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ነው
የሸካ ህዝቦች ልማት ማህበር የጀመረው የሰንበት ገቢያ በበዓል ወቅት ከሚፈጠረው የዋጋ ንረት ታድጎናል ሲሉ የሸካ ዞን ማሻ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።