ሙስና የተበላሸ አስተሳሰብ፣ ባህልና አሰራር ውጤት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።የፌዴራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የብሔራዊ የሙስና ወንጀል መረጃ ጥቆማ የዲጂታል አሰራር ሥርዓት መተግበሪያ ማስጀመሪያ መርሐግብር በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት÷ ሙስና የተበላሸ አስተሳሰብ፣ ባህልና አሰራር ውጤት ነው።በተለያዩ መንገዶች የሚከናወነው የጥቆማ አሰጣጥ ሁሉንም ዜጋ የሚያሳትፍና በተለያዩ የሙስና ወንጀል ደረጃዎች ተከፋፍሎ የማጣሪያ አካሔዶችን እንደሚያልፍ ተጠቁሟል።መተግበሪያው ከእጅ ስልክ ጀምሮ በመስሪያ ቤቶች በሚኖሩ ኮምፒውተሮች በመጠቀም የሚከናወን ሲሆን የመከታተያና የማጣሪያ አካሔድ እንደሚኖርም ነው የተገለጸው።መተግበሪያው ጥቆማዎችን በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ፣ ሶማሊኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች መስጠት የሚያስችል እንደሆነም ተመላክቷል።በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀው የዲጂታል አሰራር አራት ወራት መፍጀቱ የተገለጸ ሲሆን ዜጎችን ያሳተፈ የጸረ-ሙስና ስራን ለማከናወን ያስችላል ነው የተባለው።
FBC
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች