የማህበሩን ይፋዊ ዓርማ ኮሚቴው አሳውቋል #ትርጓሜዎችን በሚመለከት#የተያያዙ እጆች ወንድማማችነትን ፣ ትብብርንና በጋራ ማደግን ፣#መሃል ክብ ውስጥ ያለው ቡና ችግኝ ልማትን/እድገትን፣እንዲሁም ካፋ የቡና መገኛ መሆኑን በተጨማሪም ጎንጋዎች በሚገኙበት አካባቢዎች ቡና በስፋት የሚመረት መሆኑን-#አረንጓዴው የተፈጥሮ ልምላሜን#ላይኛውና በታችኛው ፅሁፍ መሀል ያለው ነጫጭ ቀለበቶች ትብብርን፣መጀጋገፍን#ቢጫ ነጠብጣብ የወንድማማችነት መጠባበቅን ያመለክታል፣ለዓመታት ሳይገናኙ ተራርቀው የቆዩት የጎንጋ ህዝቦች ተገናኝተዉ በአንድነት ይመክራሉ።የእርስ በርስ ግንኙነትና ትብብርን በማጠናከር ነገን የተሻለ ለማድረግ ይመካከራሉ።ሁላችሁም የጎንጋ ህዝቦች እና ወዳጆች በዚህ ታሪካዊው የፎረም ቀን እንዲትገኙ አዘጋጅ ኮሚቴው ይጋብዛቸዋል ።
የጎንጋ ህዝቦች ልማትና ትብብር ፎረም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቴፒ ከተማ በመስከረም 25 እና 26/2017 ዓም ይካሄዳል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች