በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የተመድ) ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከኡጋንዳ እና ርዋንዳ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ ከኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሊቪየር ኑሁንጊሬሄ እና የርዋንዳ ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ከርዋንዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጋ ጋር በነበራቸው ውይይት በናይል የውሃ ሃብት ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ሁለቱ ሀገራት ስላላቸው የጋራ አቋም ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
ከኡጋንዳው አቻቸው ጋር በነበራቸው ውይይትም በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የሰላም ሁኔታ ላይ የመከሩ ሲሆን፤ በድህረ በሶማሊያ ከአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች እና አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በሶማሊያ ሰራዊት አሰማርተው የነበሩ በመሆናቸው ድህረ አትሚስ ሽብርተኝነትን በመዋጋት የተመዘገበው ውጤት ወደኋላ በማይመልስ መልኩ መፈጸም እንዳለበት መክረዋል።
በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ኡጋንዳ የምታስተናግደው የናይል ጉባዔ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ወደ ተግባር እንዲገባ የሚያስችሉ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት አምባሳደር ታዬ ገልጸዋል።
FBC
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች