ቱርክ በመዲናዋ አንካራ በ6 ሚሊየን ዶላር ለሶማሊያ ኤምባሲ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗ ተገልጿልቱርክ የሶማሊያን የባህር ክልል ከውጭ ከሚሰነዘር ስጋት ለመከላከል በመጪው ወር የጦር መርከቦቿን በአካባቢው ልታሰማራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በተያዘው የፈረንጆቹ አመት መጀመርያ የመከላከያ ስምምነትን የተፈራረሙት ሞቃዲሾ እና አንካራ በሁለትዮሽ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡ ቱርክ በቀጣዩ ወር በሶማሊያ የባህር ክልል ታሰማረዋለች የተባለው የባህር ሀይልም የዚህ የመከላከያ ስምምነት አንድ አካል ነው፡፡ወደ ቀጠናው የሚመጡት ሁለት አይነት መርከቦች ሲሆኑ አንድኛው አንካራ በአካባቢው ለምታደርገው የነዳጅ ማውጣት እንቅስቃሴ የሚያግዝ ሲሆን ሌሎቹ ድግሞ የሶማሊያን የባህር ክልል እና የነዳጅ አውጭ ቡድኑን የሚጠብቁ ናቸው ተብሏል፡፡
Al-Ain
More Stories
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች
ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የጠፈር ጣቢያዋን ለውጭ ሀገር ጠፈርተኞች ክፍት አደረገች