ኢትዮጵያ እና ቻይና ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ።በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም፣ የኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ የጥቁር አንበሳ የላቀ ጀብዱ ሜዳይ ተሸላሚ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተመራ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ የ11ኛው የቤጂንግ ሻንሻን ፎረም እየተሳተፈ ነው።‘ለጋራ ወደፊት ሰላምን ማስተዋወቅ’ በሚል መሪ ሀሳብ በቻይና በተዘጋጀው የ11ኛው የቤጂንግ ሻንሻን ፎረም እየተካሄደ ነው።በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ የተመራው የልዑካን ቡድን ከፎረሙ ጎን ለጎን ከቻይና ወታደራዊ ጥምር ኃይል አዛዥ ጀነራል ሉኤ ዠን ሊ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂዷል፡፡በውይይቱ ሁለቱም ወገኖች በአምስተኛው ትውልድ ዋር ፌር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በወታደራዊ ቁሳቁስና በወታደራዊ አቅም ግንባታ ረገድ ተባብረው ለመስራትና ትብብራቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡በውይይቱ ማጠቃለያ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ጀነራል ሉኤ ዠን ሊና መግባባት የደረሱባቸውን ጉዳዮች ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡በፊልድ ማሻሉ የተመራው ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ በፎረሙ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያደረገው ተሳትፎ ውጤታማና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን የማድረግ አቅም ለማሳደግ የሚያስችል ድጋፍን ያስገኘ ሆኖ መጠናቀቁን በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
FBC
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች