በሕገ-ወጥ ተግባር ላይ በተሰማሩ ከ7 ሺህ 600 በሚበልጡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በተደረገ ክትትል እና ቁጥጥር በሕገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው በተገኙ 7 ሺህ 676 ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው በተደረገ የገበያ ክትትል እና ማረጋጋት ሥራ እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ አለአግባብ ዋጋ በጨመሩ 7 ሺ 312 ተቋማት ላይ የማሸግ እንዲሁም በ42 ተቋማት ላይ ፈቃድ የማገድ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡ በተመሳሳይ የ36 የንግድ ተቋማት ፈቃድ ሲሰረዝ፣ በ286 ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ደግሞ የእስራት ቅጣት ተጥሏል፡፡የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ መመሪያ ትግበራ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ የሚደረገው ክትትል እና ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
EBC
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች