የሸካ ማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ተጨማሪ የሬዲዮና ቴሌቪዥንና ስቱዲዮ ጌጫ ከተማ ላይ ከፍቷል።
የሸካ ማህበረሰብ ሬዲዮና ቴለቪዥን ድርጅት ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆንም በሦስት ቋንቋዎች ማለትም በሸክኛ፣በኦቶ ማጃንግ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ከዚህ ቀደም በሳምንት ሁለት ቀን ሲያስተላለፍ የነበረውን መረጃ ወደ ሦስት ቀን በማሳደግ ለአድማጭ ተመልካቹ መረጃዎችን ተደራሽ እያደረገ ይገኛል።
የሸካ ማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ታምሩ ጎዱ እንደገለጹት ከማሻ በተጨማሪ ከዚህን ቀደም በቴፒ ከተማ ላይ ተጨማሪ ስቱዲዮ በመክፈት መረጃዎችን ተደራሽ ሲደረግ እንደነበር ገልጸው አሁን ላይ በአንድራቻ ወረዳ በጌጫ ከተማ ላይ ሶስተኛ ስቱዲዮ መከፈቱን ተናግረው ማንኛውም አካል በቅርበት መገልገል እንደሚችልም ጠቁመዋል።
ወቅታዊ መረጃዎች፣ አስተማሪና አዝናኝ ኘሮግራሞችን ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩት አቶ ታምሩ ይበልጥ እንዲጠናከር የሰው ሀይል ማፍራት ላይ ትኩረት መደረጉን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ለአዳዲስ ሠራተኞች በምስል ፣በድምፅ ፣በይዘት እና ኤዲትንግ ዙሪያ በተለያዩ ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና መሠጠቱ ለቀጣይ ዕቅድ ወሳኝ መሆኑን አንስተው በዚህም ራስን ለስራ ማዘጋጀት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
ሚዲያ በባለድርሻ አካላት ካልተደገፈ በህዝቡና በመንግስት መካከል ድልድይ የመሆን ዓላማውን ማሳካት ስለማይችል ለመረጃ ልውውጥ ሁሉም ተባባሪ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል ።
የስልጠና ተካፋይ ባለሙያዎች በበኩላቸው በምስል ፣በድምፅ ፣በይዘት እና ኤዲትግ ዘርፍ ለተከታታይ ቀናት ስራ ለመጀመር የሚያስችል ስልጠና ማግኘታቸውን ገልፀው በመረጃ የዳበረ ማህበረሰብ እንዲፈጠር በትኩረት እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።
የሸካ ማህበረሰብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ማለትም በሦስት ቋንቋዎች በማሻና በቴፒ ከተማ ላይ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ በአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ላይ ተጨማሪ ስቱዲዮ መከፈቱ የመረጃ እጥረትን ከመቅረፍ ባለፈ የአካባቢውን ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ሀብቶችን ለማስተዋወቅ ያግዛል ተብሎም ይጠበቃል።
More Stories
አዛውንቶች የሚገደሉበትና ንብረት የሚዘረፍበት ተግባር የትግል ዓላማ ሊሆን አይችልም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በቁልቢ እና በሐዋሳ እየተከበረ ነው
ኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በስፋት ያሰባሰባቸው አጀንዳዎች፣ ሕዝቡ በአንድነትና በወንድማማችነት ለመኖር ያለውን የጸና ፍላጎት በግልጽ የሚያመላክቱ መሆናቸውን ምሁራን ገለጹ።