August 3, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ቻይና ከ53 የአፍሪካ ሀገራት የምታስገባቸውን ምርቶች ከቀረጥ ሙሉ በሙሉ ነጻ ልታደርግ ነው

ማሻ ፣ የሰኔ 06፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ‎‎ ቻይና ከ53 የአፍሪካ ሀገራት የምታስገባቸውን ምርቶች ከቀረጥ ሙሉ በሙሉ ነጻ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በቻይና-አፍሪካ ስብሳባ ላይ አስታውቃለች።

ከዚህ ቀደም የቻይና የቀረጥ ነጻ እድል ተጠቃሚ የነበሩት 33 የአፍሪካ ሀገራት ብቻ እንደነበሩ ይታወሳል።

የአፍሪካ ሀገራት ወደ አሜሪካ በሚልኳቸው ምርቶች ላይ የቀረጥ ጭማሪ ሊያጋጥማቸው ይችላል በተባለባት በዚህ ወቅት፣ ቻይና ይህን ውሳኔ ማሳለፏ ለአፍሪካ ሀገራት አማራጭ የሚሰጥ እድል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

አፍሪካዊቷ ሀገር ኢስዋቲኒ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥራትን ታይዋንን ነጻ ሀገር አድርጋ ዕውቅና በመስጠቷ ከዚህ እድል ተጠቃሚ እንደማትሆን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

ቻይና ላለፉት 15 ዓመታት የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛዋ የንግድ አጋር ሆና ቆይታለች፡፡

እ.አ.አ በ2023 ከአፍሪካ ሀገራት ወደ ቻይና 170 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች ተልከዋል።

ኢቢሲ