ማሻ ፣ የግንቦት 20፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎች ቀልጣፋ እና ውጤታማ የስራ ተግባቦት እንዲፈጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ገለጹ።
በ10 የፌደራል ተቋማት፣በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የተገነቡ ስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎች ተመርቀው በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
የስማርት ኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎቹ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉ ባለድርሻ አካላትን በቀላሉ እንዲገናኙና ስራቸውን እንዲያሳልጡ የሚያስችሉ ናቸው።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ይህንን ስኬት እንዲመዘገብ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎቹ ለመረጃ ልውውጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል።
ማዕከላቱ ውጤታማ የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር በማድረግ አስፈላጊ የሆነ ፈጣን ተግባቦት እንዲፈጠር የሚያግዙ መሆኑን ገልጸዋል።
ለአመራር ሰጭ አካላትም ፈጣን የሆነ ውሳኔ ለመስጠትም ያስችላሉ ነው ያሉት።
በቀጣይም እነዚህን ማዕከላት በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስማርት የኮሙኒኬሽን ስርዓትን ለማጠናከር አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ማዕከላቱ ውጤታማ የዲጅታል ኮሙኒኬሽን ስርዓትን መፍጠራቸውን አንስተዋል።
More Stories
የማህበራዊ ሚዲያው ተፅዕኖ የጎላበት ምህዳር ተፈጥሯል- የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ።
የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ተልዕኮቸውን በሀላፍነት እና በዕውቀት እንዲወጡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ።
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ በድህረገጽና በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።