May 20, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፕሬዚዳንት ፑቲን ጦርነቱን ማቆም ይፈልጋሉ፡- ፕሬዚዳንት ትራምፕ

ማሻ ፣ የግንቦት 12፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ጉዳይ ላይ በስልክ ከተወያዩ በኋላ ፑቲን ጦርነቱን ማቆም እንደሚፈልጉ እና ይህንንም ከውይይታቸው መረዳት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡

“ጦርነቱ እንዲቆም ፕሬዚዳንት ፑቲንን ጠይቄያቸዋለሁ፤ እርሳቸውም ይህ ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲያበቃ እንደሚፈልጉ ነግውኛል” ሲሉ ጉዳዩን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ስለ ዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ “ዘለንስኪ ጠንካራ ሰው ነው፤ እሱም ይህ ጦርነት እንዲያበቃ ይፈልጋል” ብለዋል ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው፡፡

ሩሲያ እና ዩክሬን በቫቲካን የተኩስ አቁም ውይይት ቢያደርጉ ጥሩ ይሆናል ያሉት ዶናልድ ትራምፕ፤ በቫቲካን ያለው የተረጋጋ ሁኔታ ለሰላም ንግግሩ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ኢቢሲ