May 20, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አሜሪካ እና ቻይና የገቡበትን የታሪፍ ሰጣ ገባ ማርገብ የሚያስችል ውይይት አደረጉ

ማሻ ፣ የግንቦት 03፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) አሜሪካ እና ቻይና የገቡበትን የንግድ ጦርነት ለማርገብ የተደረገዉ ዉይይት በስምምነት ማብቃቱን የሀገራቱ ልዑካን ቡድኖች አስታዉቀዋል።

ከገቡበት የታሪፍ ሰጣ ገባ በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ፊት ለፊት የተገናኙት የሁለቱ ሀገራት ልዑካን፤ ወሳኝ የሆኑ ነጥቦች ላይ ከስምምነት መደረሱን ነዉ የገለፁት።

በስዊዘርላንድ ጄኔቭ ለሁለት ቀናት የተደረገዉ ዉይይት “ለዓለም መልካም ዜና የያዘ ነዉ” ሲሉ የቻይና ምክትል የንግድ ሚኒስትር ሊ ቼንግጋንግ ተናግረዋል።

የአሜሪካ የንግድ ሚኒስትር ስኮት ቤሴንት በበኩላቸው ጠንካራ እና ገንቢ ንግግር መደረጉን አንስተዋል።

የዉይይቱ ዝርዝር ነጥቦች በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ በማስታወቅ፤ ሁለቱም ወገኖች ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በቀጣይ አዲስ የምክክር መንገድ ለመከተል ማሰባቸዉንም ጠቁመዉ፤ የኢኮኖሚ ዉይይት መድረክ እንደሚኖራቸዉ አያይዘዉ ጠቅሰዋል።

ሀገራቱ የደረሱበት የንግድ ስምምነት በተጋነኑ ታሪፎች ምክንያት በሁለቱም በኩል ሊደርስ የሚችል የንግድ ጫናን ማቃለል የሚችል እንደሆነ መገልጹንም ሮይተርስ በዘገባዉ አስታውሷል።

ኢቢሲ