April 14, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው በሊድስ ዩናይትድ ተሸነፈ

ማሻ፤ ሚያዝያ 6/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊድስ ዩናይትድ ማንቼስተር ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኦልድትራፎርድ በተካሄደው ጨዋታ የሊድስ ዩናይትድን ሁለቱንም የማሸነፊያ ግቦች ኦካፎር አስቆጥሯል።

ማንቼስተር ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ካስሚሮ ከመረብ አሳርፏል።

በጨዋታው የማንቼስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።