ማሻ፤ መጋቢት 10/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የቴፒ ከተማ አስተዳደር 1447ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ80 አቅመ ደካማ ሙስሊም ወገኖች 160 ሺ ብር የሚያወጣ የምግብ ዘይትና የዱቄት ድጋፍ አድርጓል ።
የቴፒ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብርሀም ወንድማገኝ እንደገለፁት ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ሁሉ ከማህረሰቡ ውስጥ አቅመ ደካማ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት ከተማ አስተዳደሩ ካለው ነገር ላይ በየዓመቱ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም አቅመ ደካሞችን መርዳት ከሁሉም ህብረተሰብ የሚጠበቅ ተግባርና ባህል ልናደርገው የሚገባ መሆኑን ገልፀዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በየጊዜው እንደሚያደርገው ሁሉ የ1447ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ 80 ለሚሆኑ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች 160 ሺህ ብር የሚያወጣ የምግብ ዘይትና የፉርኖ ዱቄት ድጋፍ ማድረጉን አክለዋል ።
ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረውና ከተማ አስተዳደሩ በዘላቂነት አቅመ ደካሞችን ከተረጂነት እንዲወጡ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የቴፒ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አለምገና አሰፋ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለፁት በየአካባቢያችን የተቸገሩ ወገኖችን በበዓላት ወቅት ብቻ ሳይሆን ሁሌም በችግራቸው ጊዜ ከጎናቸው በመሆን እገዛ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል ። ዘገባው የቴፒ ከተማ መ/ኮ/ጉ/ ነው።
የቴፒ ከተማ አስተዳደር 1447ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ80 አቅመ ደካማ ወገኖች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ ።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች