ማሻ፤ የካቲት 27/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የአሜሪካ ግምጃ ቤት ህንድ ነዳጅ ከሩሲያ እንዳትገዛ ጥሎት የነበረውን እገዳ ለ1 ወር ማንሳቱን አስታውቋል።
እገዳው ህንድ ገዝታው በባህር ላይ በእግድ ምክንያት ሳይንቀሳቀስ የቆየውን የሩሲያን ነዳጅ እንድታስገባ የሚያስችል ነው ተብሏል።
የግምጃ ቤቱ ሃላፊ ስኮት ቤሴንት በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ እርምጃው ነዳጅ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲገባ ያደርጋል ብለዋል።
እገዳው ቀድሞ መንገድ ላይ ለነበረ ነዳጅ የተነሳ በመሆኑ ለሩሲያ እምብዛም ጥቅም እንደማያስገኝም ገልጸዋል።
ለአጭር ጊዜ እንዲቆይ የተደረገው ሆን ተብሎ መሆኑን በመጥቀስም፥ ወደፊት ህንድ ከአሜሪካ የምትገዛውን ድፍድፍ ነዳጅ መጠን ታሳድጋለች ብለው እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።
አሜሪካ ህንድ የሞስኮን ነዳጅ እንዳትገዛ ጫና በመፍጠር የሩሲያን የገንዘብ ምንጭ ለመቀነስ እየሞከረች ትገኛለች።
በመካከለኛው ምስራቅ አሜሪካ እና እስራዔል በኢራን ላይ የጀመሩትን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ የዓለማችን ዋነኛ የነዳጅ መተላለፊያ የሆነው የሆርሙዝ ባህር ወሽመጥ በመዘጋቱ ሳቢያ በዓለም አቀፉ የነዳጅና ጋዝ ዋጋ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተከስቷል።
More Stories
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ተሾሙ
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የጠፈር ጣቢያዋን ለውጭ ሀገር ጠፈርተኞች ክፍት አደረገች
ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚላመድና የማይበገር የልማት ግስጋሴዋን በተጨባጭ ውጤቶች እያስመሰከረች ቀጥላለች።