በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ በርንሌይን 1 ለ 0 አሸንፏል። በተርፍ ሙር በተደረው ጨዋታ ሃለንድ የሲቲን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።
ማንችስተር ሲቲ ከነሀሴ ወር በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ከአርሰናል ተረክቧል። ሲቲ ከአርሰናል ጋር እኩል 70 ነጥብ እና እኩል የግብ ክፍያ ቢኖራቸውም ብዙ ግብ በማስቆጠር በልጦ ሊጉን መምራት ጀምሯል።
እስካሁን ማንቸስተር ሲቲ ያስቆጠራቸው ግቦች 66 ሲሆኑ፣ አርሰናል ደግሞ 63 ግቦችን አስቆጥሯል።
በርንሌይ ዎልቭስን ተከትሎ ከፕሪሚየር ሊጉ የወረደ 2ኛው ክለብ ሆኗል።
More Stories
“መድፈኞቹ የሊጉን ዘውድ ይደፋሉ” አርሰን ቬንገር
አርሰናል እና ባየር ሙኒክ ለግማሽ ፍጻሜ ደረሱ
ፖርተኞች ፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት በመላበስ ውድድር ማካሄድ እንዳለባቸው የዉድድሩ ስነስርዓት ኮሚቴ ገለፀ።