የደ/ም/ኢ/ህ/ ክልል ጤና ቢሮ በሸካ ዞን ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የመስክ ምልከታ አካሄዷል ።
በHIV AIDS በሽታን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የአምራች ዜጎችን ህይወት መታደግ የሁሉም ድርሻ መሆን እንዳለበትም ተመላክቷል ።
የመስክ ምልከታ ቡድን ከዞን ጤና መምሪያ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በየኪ ወረዳ በጪ፣በአንድራቻ ወረዳ ጌጫና በማሻ ከተማ አስተዳደር የማሻ ጤና ጣቢያዎች የHIV AIDS በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ዙራያ የመስክ ምልከታ አካሂዶ ጠንካራና መሻሻል ያለባቸዉ ጉዳዮችን በመለየት ግብረ መልስ ሰጥቷል ።
የማሻ ጤና ጣቢያ የHIV AIDS በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እያተከናወነዉ ያለዉ ተግባር ጥሩ ተሞክሮ ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙት በክልሉ ጤና ቢሮ የHIV AIDS በሽታን መከላከልና መቆጣጠር በCDC ፕሮጀክት የHIV Care and Treatment Adviser ዶክተር እመቤት ከተማ የHIV ጥንቃቄና እንክብካቤ እንድሁም የVCT አግልግሎት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ።
ከ0.5% የAIDS ፈንድ 925,000 ብር ተሰብስቦ ኦዲት እየተደረገ ለ8 ሰዎች ቫይረሱ በደማቸዉ ለሚገኘዉ ወገኖች እየተከፈለ መሆኑ በጠንካራ ጎን የሚታይ ነዉ ሲሉ በክልሉ ጤና ቢሮ የHIV AIDS መከላከልና መቆጣጠር ስራ ሂደት የCDC ፕሮጀክት የHIV ምርመራ አማካሪና የMTCT ፎካል አቶ የኋላሼት ተመዝገን ተናግረዋል
በሌላ በኩል የክልኒካል ኦፊሰር ያለመኖር፣የኮንዶም ስርጭት ዝቅተኛ መሆንና የተሰሩ መረጃዎችን በወቅቱ ሪፖርት ከማድረግ አንፃር ያሉ ክፍተቶች እንድሁም HIV ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የማሻ ከተማ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሌሳ መኮንን በክልሉ ጤና ቢሮ የተደረገዉን የመስክ ምልከታ አድንቀዉ፡የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ክፍተቶችን ለማረም በትኩረት እንሰራለን ብለዋል ።
በተለይ የHIV AIDS ምርመራ ለማድረግ ማነቆ የሆኑ የባለሙያና የግባት እጥረት ለሟሟላት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ ገልፆ ክልሉም በስልጠና እንዲያግዛቸዉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
More Stories
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ተሾሙ
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የጠፈር ጣቢያዋን ለውጭ ሀገር ጠፈርተኞች ክፍት አደረገች
ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚላመድና የማይበገር የልማት ግስጋሴዋን በተጨባጭ ውጤቶች እያስመሰከረች ቀጥላለች።