ማሻ፤ የካቲት 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ጣቢያው የተመሠረተበትን ሁለተኛ ዓመት በዓል ምክንያ በማድረግ ከጠዋቱ 1:00 – ቀን 6:00 ሰዓት የነበረውን ከ 1: 00 እስከ 8:00 እንዲሁም ከ 12:00 እስከ 4:00 ሰዓት የነበረውን የምሽት ስርጭት ከቀኑ 11:00 እስከ ምሽት 4:00 መራዘሙን የጣቢያው
ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የይዘት ዘርፍ ኃላፊ ታደሰ ጋረፎ አብስረዋል።
የመረጃና መዝናኛ ዝግጅቶችን ተደራሽነት ለማስፋት የስርጭት ሰዓቱን በቀን ወደ 12:00 ለማሳደግ መንስኤ የሆኑት የጣቢያው ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ሊመሰገኑ ይገባልም ብለዋል።
ወቅቱን የሚመጥኑ ይዘቶችን በማዘጋጀት በተሻለ አቀራረብ አድማጭን ለማርካት በአማርኛ፣ ሸኪኛ እና በማጃንግ ቋንቋዎች እንደሚሰናዳም አቶ ታደሰ አውስተዋል።
መረጃ በመስጠት፣ በቀጥታ ስርጭት በመሳተፉ ለጣቢያው ሁለንተናዊ ለውጥ እገዛና ብርታት እየሆኑ ላሉት አድማጮችና ባለድርሻ አካላት ምስጋና ያቀረቡት የጣቢያው ስራ አስኪያጅ ታምሩ ጎዱ ናቸው።
በማሻሻያው ላይ አስተያየት የሰጡት የጣቢያው ሰራተኞች በታሪክ አጋጣሚ እጃችን ላይ የገባውን ሚዲያ ሀያልነት ማዕከል ያደረገ ስራ በመስራት ይበልጥ ተመራጭ ለመሆን እንሰራለን ብለዋል።
More Stories
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከጥገኝነት ወደ ልዕልና
የማይክል ጃክሰን የሕይወት ታሪክ ፊልም የዓለምን የቦክስ ኦፊስ ክብረ ወሰን ሰበረ
ለተከታታይ አምስት ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት ነው