ማሻ፤ የካቲት 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የፓርቲው አባላትና አመራሮች 7ኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በጌጫ ከተማ ሰጥቷል
ፓርቲው 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ”ሰላም ለሁሉም ፤ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ፖለቲካዊ ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለአባላቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በመድረኩ የተገኙት በሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ገቦ እንደተናገሩት ፓርቲው በጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመጣመር እየተፎካከረ ይገኛል ብለዋል።
ምርጫው ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ፓርቲው እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል አቶ ዮሐንስ።
ጥምረቱ የተፎካካሪነት አቅም እንዲጎለብት ያግዛል ያሉት አቶ ዮሐንስ የተለያዩ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በዝርዝር አቅርበዋል።
የሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት አቶ አዲሱ አምበሎ በበኩላቸው የፓርቲው አመራሮችና አባላቱ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲሳተፉና በፓርቲው የተለያዩ እሳቤዎች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።
የሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የመወዳደሪያ ምልክት ቡና ሲሆን እርግብ የጥምረቱ አርማ መሆኑም ተገልጿል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች