ማሻ፤ የካቲት 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ በዞኑ ቴፒ ከተማ የ7ኛዉ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ማኒፈስቶና የምርጫ ምልክት ትዉዉቅ መድረክ በዞኑ ቴፒ ከተማ የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ አባላትና የፓርቲዉ ደጋፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል ።
በመድረኩ የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለማየሁ ዓለሙ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ብዙ እምቅ አቅም ያላት ሀገር ብትሆንም በርካታ መሠራት ያለባቸዉ ጉዳዮች መኖራቸዉን አንስተዋል።
በዚህም ህብረ ብሔራዊነትን ለማጽናት፣ድህነትና ኋላ ቀርነትን ለመቅረፍ፣ የዉስጥና የዉጭ ግጭትና ጦርነትን ለማስቀረት ብሎም ሌሎችንም ችግሮች ለመቅረፍ የብልጽግና ፓርቲ ይሠራል ብለዋል።
የኢትዮጵያን የባህር በሯን ለማስመለስና ሌሎችንም ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ እየተሠራ ነዉም ብለዋል።
የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ኢትዮጵያ ብዙ ተስፋ ያላት የብዙ ታሪክ ባለቤትና ዕድሜ ጠገብ ሀገር መሆኗን አንስተው ሁሉም ዜጎች እኩል የሚጓዙበት ብሔራዊ ራዕይ እንዲኖር ፓርቲያቸዉ እንደሚሠራም ተናግረዋል።
በሰላም ረገድ በተሰራዉ ትልቅ ተግባር ዛሬ ላይ ሸካ ዞን በሰፊዉ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እየሆነ እንዳለ አንስተዋል።
ቀጣይነት ያለዉ ግዙፍ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ፓርቲዉ እንደ ሀገር እየሠራ እንዳለም አቶ አበበ ማሞ አስታዉሰዋል።
የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል ሰፊ ርብርቦች እየተደረገ እንዳለ ተናግረዋል።
የፓርቲያቸዉ ምልክቱም የስንዴ ነዶ መሆኑንና ምልክቱም የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል።
የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ምርጫ ማኒፈስቶና የምርጫ ምልክት ትዉዉቅ መድረክ
More Stories
የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት ዳግም ያረጋገጡ አዲስ የአርኪዮሎጂ ግኝቶች…
በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት የበልግ ተጠቃሚ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ ተባለ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ከኢራን ጋር ድርድር ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ