ማሻ፤ ጥር 09/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ ግብጽን በማሸነፍ 3ኛውን ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች።
ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ መደበኛ የጨዋታ ጊዜ አልቆ በመለያ ምት ናይጄሪያ ግብጽን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡
ይህንን ውጤት ተከትሎም ናይጄሪያ በውድድሩ 3ኛ ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ ግብጽ 4ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች።
የአፍሪካ ዋንጫ በነገው ዕለት ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን፥ አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ ከሴኔጋል ጋር ለዋንጫው ይፋለማሉ።
More Stories
አርሰናል ከ20 ዓመት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ ደረሰ
ማንቼስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋገጠ
ኬንያዊው አትሌት በሽልማት ተንበሸበሸ