February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በ2017 ዓ/ም በሸካ ዞን ጌጫ ከተማ ለውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ የተከማቹ ጠጠሮች ባለመበተናቸው ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ

ማሻ፣ ታህሳስ 27/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የአንድራቻ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ ነዋሪዎቹ ያነሱት ቅሬታ ተገቢ መሆኑን በመግለጽ ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።

‎በጌጫ ከተማ በተለያዩ መንደሮች ተገኝተን ካነጋገርናቸው ነዋሪች መካከል ወ/ሮ ውድነሽ ከበደ፣ አቶ አጥናፉ አመያ እና መ/ር አመነ አሰፋ እንደተናገሩት በ2017 ዓ/ም በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተከፈቱና ጥገና የተደረገባቸው የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ተስፋ ሰጪ እንደነበሩ አንስተዋል ።

‎ይሁን እንጂ በመንደራቸው የተከማቸ ጠጠር ባለመበተኑ ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ እንደሆነ ተናግረዋል ።

‎ጣቢያችን ጉዳዩን አስመልክቶ ከወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሳምነው አይኔ ጋር ባደረገው ቆይታ አስተዳዳሪው እንዳነሱት ቅሬታው ተገቢ መሆኑንና በቅርቡ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል።

‎በ2018 በጀት ዓመት የከተማ መሠረተ ልማትን ለማሳለጥ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ በቅርቡ ወደ ስራ የሚገባ እንደሆነ አስረድተዋል ።

‎አስተዳዳሪው በየዓመቱ በተለያዩ የልማት ተግባራት ላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረው በተያዘው በጀት ዓመት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።