ማሻ ፣ የግንቦት 12፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ጉዳይ ላይ በስልክ ከተወያዩ በኋላ ፑቲን ጦርነቱን ማቆም እንደሚፈልጉ እና ይህንንም ከውይይታቸው መረዳት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡
“ጦርነቱ እንዲቆም ፕሬዚዳንት ፑቲንን ጠይቄያቸዋለሁ፤ እርሳቸውም ይህ ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲያበቃ እንደሚፈልጉ ነግውኛል” ሲሉ ጉዳዩን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
ስለ ዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ “ዘለንስኪ ጠንካራ ሰው ነው፤ እሱም ይህ ጦርነት እንዲያበቃ ይፈልጋል” ብለዋል ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው፡፡
ሩሲያ እና ዩክሬን በቫቲካን የተኩስ አቁም ውይይት ቢያደርጉ ጥሩ ይሆናል ያሉት ዶናልድ ትራምፕ፤ በቫቲካን ያለው የተረጋጋ ሁኔታ ለሰላም ንግግሩ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ኢቢሲ
More Stories
ትራምፕ ቲክ ቶክን የሚገዙ የአሜሪካ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን ገለፁ
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ