June 20, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አፍሪካ በሀገር በቀል አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማሻ ፣ የግንቦት 09፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው “አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ለአፍሪካ” መርሃ ግብር ላይ፥ አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ወደ አዲስ ዘመን እየተሻገረች መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው አንሰተዋል።

ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና የክሂሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት እየመራች መሆኑን አውስተዋል።

እንደ ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲቲዮት፣ ዲጂታል መታወቂያ ብሎም “የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ” ባሉ ፕሮግራሞቿ ኢትዮጵያ ሕልሞቿን ወደ ተጨባጭ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተግባራት መለወጥ ችላለች።

በ2030 ማንም ወደ ኋላ በማይቀርበት አኳኋን አፍሪካ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን በራሷ መልክ በሥነምግባር፣ በአካታችነት እና ዘላቂነት ቅርፅ ማስያዝ እንደሚኖርባት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስምረውበታል።