May 12, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ“ቴክ ቶክ ከሰለሞን ጋር” በክፍል አንድ በነበራቸው ቆይታ ካነሷቸው በርካታ ጉዳዮች መካከል፡-

ማሻ ፣ የግንቦት 02፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ዕውቀት ችግር እስካልፈታ ድረስ በዕውቀት መስፈርት ውስጥ ሊታይ የሚያስችል ብቃት አይኖረውም።

👉 በኢትዮጵያ እስከ ቀጣይ ዓመት ድረስ በአጠቃላይ ወደ 55 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው፤ ይህም ይህም በዓለም ላይ ትልቁ የደን ማልማት ሥራ ይሆናል፡፡

👉 ከሌሎች ሴክተሮች ዕቅድ አንጻር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል፡፡ አሁን ላይ ለዲጂታል 2030 ዝግጅት እየተደገ ነው፡፡

👉 በሀገራችን ቴክኖሎጂ በሲቪል ሰርቪስ፣ በሕግ ማስከበር፣ በመከላከያ፣ በሚዲያ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ ዘርፎች ያሉ ሥራዎችን ለማሳካት እና ለማሳለጥ ጥቅም ላይ እዋለ ነው፡፡

👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመት ከ100 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን ማጓጓዝ የሚያስችል ዕቅድ እና ለዚህም የሚያግዘውን አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እየሠራ ነው፡፡

👉 በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ሎጂስቲክስ የሚያጓጉዙ ድሮኖች እንዲሁም በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) የሚንቀሳቀሱ ተዋጊ ጀቶች ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ።

👉 ከዓመታት በፊት የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት በአፍሪካ በጣም ውድ ነበር፤ አሁን ላይ ግን በአህጉሪቱ በዝቅተኛ ዋጋ አገልግሎቱን ማቅረብ ተችሏል፡፡

👉 በአሁኑ ወቅት 51 ሚሊየን ገደማ ሰዎች የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

👉 የሰው ሠራሽ አስተውሎት(አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ – ኤ አይ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በፒኤችዲ ደረጃ መሰጠት ተጀምሯል።

👉 በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከ“ቻት ጂፒቲ” ወይንም “ዲፕ ሲክ” ጋር ተመሳሳይነት ያለው “መላ” የተሰኘ የሀገር ውስጥ ቋንቋን በስፋት የሚጠቀም የኤአይ ሥርዓት ተገንብቷል፡፡

👉 የአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) ሰሚት በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል። በዚሁ ወቅት 1 ሺህ ገደማ ድሮኖች በኤአይ ታግዘው ትርዒት ያቀርባሉ፡፡

👉 የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ ውስጥ ቀዳሚ ሚና አለው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮም ሁሉ የአፍሪካውያን ኩራት መሆን ይችላል።

ፋና