ማሻ ፣ የመጋቢት 29፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የፓስፖርት አገልግሎት ደንበኞችን በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ተጠርጣሪዎቹ አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን የሚል ማታለያ በመጠቀም በ24 የአገልግሎቱ ደንበኞች ላይ የማጭበርበር ወንጀል መፈጸማቸው ተጠቅሷል፡፡
የወንጀል ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎች ተቋሙ ለ5 ቀን 20 ሺህ ብር የሚያስከፍለውን 28 ሺህ ብር ሲያስከፍሉ መቆየታቸውም ነው የተገለፀው፡፡
አገልግሎቱ ከፌደራል ፓሊስ እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በቅንጅት ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው፣ ተገልጋዮቹ የከፈሉት ገንዘብ እንዲመለስ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
ደንበኞች ከመሰል የማጭበርበር ተግባር ራሳቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም ስለአገልግሎቱ ማንኛውም አይነት መረጃ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመረጃ ዴስክ አልያም ከተቋሙ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲያገኙ አገልግሎቱ አሳስቧል፡፡
ኢቢሲ
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ