May 6, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ በፊፋ ደረጃ 147ኛ ሆናለች

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

ፊፋ ባሳወቀው የመጋቢት ወር የሀገራት የወንዶች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ደረጃ መሰረት በቅርቡ ግብጽ እና ጅቡቲን የገጠመችው ኢትዮጵያ አንድ ደረጃ ዝቅ በማለት 147ኛ ላይ ተቀምጣለች፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ2026 አለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች መጋቢት ወር ላይ ከግብጽ እና ጅቡቲ ብሄራዊ ቡድኖች ጋር መጫወቱ የሚታወስ ነው፡፡

ሞሮኮ ላይ በተካሄዱት ጨዋታዎች ዋልያዎቹ በግብጽ 2ለ0 ሲረቱ ከቀናት በኋላ ደግሞ ጅቡቲን 6ለ1 ማሸነፋቸው ይታወቃል፡፡

አቡበከር ናስር እና በረከት ደስታ በጅቡቲው ጨዋታ እያንዳንዳቸው ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራታቸው የቅርብ ቀናት ትውስታ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ የነጥብ ጨዋታ ያደረገው ታህሳስ ላይ በቻን ማጣሪያ ከሱዳን ጋር እንደነበር ይታወሳል፡፡

በወቅቱም የመሳይ ተፈሪ ቡድን በድምር ውጤት 4ለ1 ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡

የመጋቢት ወር ጨዋታዎችን ተከትሎ ፊፋ ይፋ ባደረገው የብሄራዊ ቡድኖች ደረጃ መሰረት ኢትዮጵያ የባለፈው ወር ከነበረበችበት ደረጃ በአንድ ዝቅ በማለት 147ኛ ላት ተቀምጣለች፡፡

የኢትዮጵያ ተጋጣሚ የነበረችው ግብጽ 32ኛ እንደዚሁም ጅቡቲ 192ኛ ናቸው፡፡

210 ሀገራት ደረጃን ይፋ ያደረገው ፊፋ አርጀንቲናን 1ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧል፡፡

ስፔን፤ፈረንሳይ፤ እንግሊዝ እና ብራዚል ከ2 እስከ 5 ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ከአፍሪካ ሀገራት ሞሮኮ 1ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ሴኔጋል 2ኛ እንዲሁም ግብጽ 3ኛ ናቸው፡፡