ማሻ ፣ የመጋቢት 26፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ልማት ማህበሩ 11 ዓመት ጠቅላላ ጉባኤን በቴፒ ከተማ እያካሄደ ይገኛል ።
የልማት ማህበሩ ሥራአስኪያጅ አቶ ሽፌራው ዳሪቶ በማህበሩ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን ሪፓርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት ማህበሩ ከተቋቋመበት ዋና አላማ አንፃር በየደረጃው ከምገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደምገኘ አመላክቷል ።
በዚህም መንግሥታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት በትምህርት በጤና እንድሁም መሠረተ ልማቶችን ለሟሟላት ልማት ማህበሩ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በማህበራዊ ዘርፍ ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራት በመፈፀም በተለይም ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን በመለየት ለትምህርታቸው የሚሆኑ ግባቶችን በሟሟላት በኩል ማህበሩ እየሰራ እንጀምገኝ ጠቁመዋል ።
በዞኑ ከአሁን በፍት ማዲያ በሌሉባቸው አካባቢዎች ነዳጅ የማዳረስ ስራ በስፋት እንደተሰራ ያመለከቱት አቶ ሽፈራው ስኳርና ሌሎች የፍጆታ እቃዎችን የማከፋፈል ስራ ተሰርቷልም ብለዋል።
ቀጣይ ህብረተሰቡን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ጥረት ሁሉም ልደግፍ እንደምገባም ሥራአስኪያጅ አሳስበዋል ።
ከጉባኤው ጎን ለጎን በልማት ማህበሩ አማካኝነት በቴፒ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የህንፃ ግንባታ በጉባኤ ተሳታፊዎች የተጎበኘ ስሆን በሌሎች አጀንዳዎች ዙርያም በመወያየት አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል ።
More Stories
የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ
700 ሱቆችን በአንድ ጣራ ስር የያዘው የዓለማችን ግዙፉ የገበያ ማዕከል
ዓለምን ያስደመመው ኢትዮጵያዊ ዲዛይነር