ማሻ፡ ጥር 04/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) በሚዛን አማን ከተማ ለቢስት ባር እሮጣለሁ በሚል መሪ ቃል የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል።
የቤንች ብሄር ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” በነገው ዕለት በድምቀት የሚከበር ሲሆን በዓሉን ምክንያት በማድረግ የጎዳና ላይ ሩጫ ተደርጓል።
በሩጫው ላይ የዞኑ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በውድድሩ ላሸነፉ ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
More Stories
አርሰናል ከ20 ዓመት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ ደረሰ
ማንቼስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋገጠ
ኬንያዊው አትሌት በሽልማት ተንበሸበሸ