July 14, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

ማሻ ፣ የሀምሌ 07፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ‎መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምክር ቤቱ የክልሉን አስፈፃሚ አካላት ተግባር በየደረጃው በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።

አክለውም የመድረኩን አላማ በማስረዳት፣ የአፈፃፀም ሪፖርቱ የምክር ቤቱን ደንብ በጠበቀ መልኩ እንዲቀርብ አሳስበው መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል።

በዚህም መሰረት ህግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር፣ ግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች፣ በጀትና ፋይናንስ፣ ከተማና መሠረተ ልማት እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች በየዘርፉ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

መድረኩ ለተከታታይ 2 ቀናት እንደሚካሄድ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በመድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፀሀይ ደርጫን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ አመራሮችና የየዘርፉ ባለሙያዎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ የደቡብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

ክልል ኮሚኒኬሽን