July 9, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ12 ሀገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እገዳ ተግባራዊ ሆነ

ማሻ ፣ የሰኔ 02፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተፈረመው እና የ12 ሀገራትን ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚገድበው የጉዞ እገዳ በዛሬው ዕለት ተግባራዊ ሆኗል።

መመሪያውም ከዛሬ ጀምሮ በሀገራቱ ላይ ተግባራዊ ሲሆን፥ በቀጥታ የታገዱት 12 ሀገራት አፍጋኒስታን፣ ምያንማር፣ ቻድ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ሄይቲ፣ ኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና የመን ናቸው።

በተጨማሪም አዲሱ መመሪያ ከቡሩንዲ፣ ኩባ፣ ላኦስ፣ ሴራሊዮን፣ ቶጎ፣ ቱርክሜኒስታን እና ቬንዙዌላ ላይ ጥብቅ የኢሚግሬሽን ገደቦችን ጥሏል።

ምንም እንኳን ዛሬ ስራ ላይ የዋለው የጉዞ እገዳ ከተጠቀሱት ሀገራት የሚመጡ ዜጎችን አዲስ የቪዛ ማመልከቻ የሚከለክል ቢሆንም፤ እገዳው ቀደም ሲል የተሰጡ ቪዛዎችን እንደማይሰርዝ መመሪያው ላይ በግልጽ ተቀምጧል።

ነገር ግን፣ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ፣ ከተዘረዘሩት አገሮች አዲስ የቪዛ ማመልከቻዎችን የሚያስገባ ገለሰብ በልዩ እና አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር ማመልከቻው ወዲያውኑ ውድቅ ይሆናል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።

ኢቢሲ