May 12, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ከቀጥታ ውይይት በፊት የተኩስ አቁም ስምምነት መኖር አለበት፦ ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ

ማሻ ፣ የግንቦት 03፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ሩስያ ለቀጥታ የሰላም ንግግሮች ያቀረበችውን ሀሳብ በደስታ በመቀበል ነገር ግን ድርድር ከመጀመሩ በፊት የተኩስ አቁም መኖር እንዳለበት አጥብቀው አሳስበዋል።

ዘሌንስኪ በኤክስ ገፃቸው ላይ፥ የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቀጥታ ውይይት ለመጀመር ያቀረቡትን ጥሪ “በጎ ምልክት” በማለት ገልፀውታል።

አያይዘውም፥ “መላው ዓለም ይህን ለረጅም ጊዜ ሲጠብቀው ቆይቷል” ብለዋል።

ሆኖም ግን ማንኛውንም ግጭት ለማስቆም የመጀመሪያው እርምጃ መሆን ያለበት የተኩስ አቁም ስምምነት ነው ብለዋል።

ኢቢሲ