የበሽር አላሳድን የ 24 አመት ስልጣን በገረሰሰው የትጥቅ ትግል ውስጥ ወሳኝ ሚና የነበረው ሙርሃፍ አቡ ቋስራ የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ ተሾሟል
የቀድሞ የሶሪያ አማጺዎች ተዋህደው በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ለመሆን መስማማታቸው ተገለጸ።
በይፋ ያልተሾመው የሶሪያ መሪ አህመድ አል ሻራ ከቀድሞ የአማጺ ቡድን ኃላፊዎች ጋር ሁሉንም ቡድኖች ለማፍርስ እና በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ለማሰባሰብ ትናንት መስማማቱን አዲሱ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ አል በሽር ሚኒስቴሩ የቀድሞ አማጺያንን እና ከበሽር አላሳድ ጦር የከዱ ወታደሮችን በመጠቀም እንደሚዋቀር ባለፈው ሳምንት ገልጸው ነበር።
ሻራ በሀገሪቱ ባሉ በርካታ ቡድኖች መካከል ግጭት እንዳይፈጠር የማድረግ ከባድ ኃላፊነት ወድቆበታል
የበሽር አላሳድን የ 24 አመት ስልጣን በገረሰሰው የትጥቅ ትግል ውስጥ ወሳኝ ሚና የነበረው ሙርሃፍ አቡ ቋስራ የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ ተሾሟል።
በሶሪያ ያሉ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የጓሳ አባላት እና የሀይማኖት ተከታዮች በእርስበርስ ጦርነቱ ወቅት የሱኒ እስላማዊ ህግ ሊመጣ ይችላል በሚል ሲሰጉ ቆይተዋል።
ሻራ እሱ የሚመራው እና የቀድሞው የአልቃኢዳ አጋር ሀያት ታህሪር አልሻም(ኤችቲኤስ) በቀድሞው አገዛዝ ላይ በቀል እንደማይፈጽም እና አናሳ ቁጥር ያላቸውን የሀይማኖት ተከታዮች እንደማይጨቁን በሶሪያ ጉብኝት ላደረጉት ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ተናግሯል።
የሶሪያ አማጺያን በጥቂት ቀናት ውስጥ በፈጸሙት መብረቃዊ ጥቃት ደማስቆን በመቆጣጠር የ 13 አመቱ የእርስበርስ ጦርነት እንዲያበቃ እና የበሸር አላሳድ ቤተሰባዊ አገዛዝ እንዲያከትም አድርገዋል። ከስልጣን የተወገዱት አሳድ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ሩሲያ ኮብልለዋል።
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።