በተመሳሳይ ቡና አምራች አርሶ አደር የወይዘሮ ምርትነሽ ታደለ በገማድሮ ቀበሌ የቡና ልማት እንቅስቃሴንም ጎብኝተዋል።
በ2010 ዓ.ም በመንግስት ድጋፍ የቡና ልማት ስራን የጀመሩ መሆናቸውን የተናገሩት ወይዘሮ ምርትነሽ ከዚህ ቀደም የእጅ ማሽን በመጠቀም እያመረቱ ውጤታማ በመሆናቸው የቡና ኢንዱስትሪ ማሽን መትከል መቻላቸውን ተናግረዋል።
በ2016/17 ዓ.ም ምርት ዘመን 1መቶ 50ሺህ ኪ.ግ የታጠበ ቡና እያመረቱ ሲሆን ምርታቸውን ለመሸጥ የገበያ ትስስር ያለመኖርና መንገድ ተግዳሮት እንደሆነባቸው ገልፀዋል።
የበለጠ ውጤታማ ለመሆን የቡና ልማታቸውን የማስፋት ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረው መንግስት የብድር አገልግሎት የሚያገኙበትን አቅጣጫ እንዲያመቻች ጠይቀዋል።
በመጨረሻም ስመለከቱ የነበረውን የተለያዩ የልማት ምርቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ግብረመልስ በመስጠት ለሁለት ቀን ስካሄድ የነበረው የልማት ጉብኝት ተጠናቋል።
በጉብኝቱም የኢፌዲሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉን ጨምሮ የዞን፣የከተማና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
More Stories
በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከልና ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ተባለ ።
ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ሁለተኛውን የዓርበኝነት ምዕራፍ ጀምራለች – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ላለው ፈጣን እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፦ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር)