ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በእምነቱ አስተምህሮ ከተጫነበት ተራራ ስር ተሰውሮ ከነበረበት ስፍራ ይወጣ ዘንድ በደመራ ሰማያዊ ምልክት የታየበት ቀን የሚከበርበት በዓል ነው ብለዋል፡፡የመስቀል በዓል የአዳዲስ እሳቤዎች የሚነገሩበት ከጨለማ ወደ ብርሃን የምንሸጋገርበት አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት የጠብ ግድግዳ የሚፈርስበት ሰላም የሚሰበክበት ብሩህ ተስፋ የሚሰነቅበት ጊዜ ነው ሲሉም ተናግረዋል ስል የዘገበው የክልሉ መ/ኮ/ጉ/ቢሮ ነው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

More Stories
ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚል የገባ ስንዴ የለም – አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የሚዘረጋቸውን የተለያዩ ኢንሸቲቦችን ቀድሞና ፈጥኖ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መታየታቸው ተገለፀ ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ6 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ