የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለሀገር ዕድገት እና ብልፅግና ወሳኝ ድርሻ አለው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ገለጹ፡፡
አቶ አሕመድ ሺዴ በቅርቡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ከኢፌዴሪ አየር ኃይል የተለያዩ ክፍሎች ከተውጣጡ የሰራዊቱ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በመድረኩ በሰጡት ማብራሪያ÷ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቁም ባለፈ የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ብለዋል።
ይህም የኢትዮጵያን ዕድገት እና ብልፅግናን ወደ ተሻለ ከፍታ እንደሚያሸጋግር ተናግረዋል።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው÷ በተቋሙ ያሉ የሰራዊቱ አመራሮች የመንግስትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በበቂ ሁኔታ መረዳታቸው ቀጣይ ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲመሩ እንደሚያስችል መጥቀሳቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
FBC
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ