ትራምፕ በመጪው ህዳር ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፔንሲልቬንያ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ነው የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው። በደጋፊዎቻቸው መሃል በመድረክ ላይ ቆመው የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያሰሙ የተተኮሰባቸው ዶናልድ ትራምፕ፤ በጆሯቸው አካባቢ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተለቀቁ ምስሎች አሳይተዋል። በወቅቱ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የግድያ ሙከራውን ያደረገው ግለሰብ ህይወት ማለፉ ተነግሯል።ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን የአሜሪካው ኤንቢሲ ኒውስ ዘግቧል።ዶናልድ ትራምፕ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው ተብሏል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ክስተቱን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ጥቃቱን አውግዘዋል።አሜሪካ ውስጥ በኃይል የሚደረግ እንቅስቃሴ ቦታ የለውም ሲሉም ተናግረዋል።ሌሎች የሀገሪቱ ባለስልጣናትና የዓለም ሀገራት መሪዎችም ጥቃቱን እያወገዙ መሆኑ ተዘግቧል።
EBC
More Stories
ሩሲያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ ከመክፈት ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበራትም – ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከፔይትሮ ሳሊኒ ጋር በሮም ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑክ ቡድናቸው በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኤሊሴ ቤተመንግሥት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።