ጀርመን የሰራተኛ ዕጥረቷን ለመፍታት በሚል ወደ ሀገሯ እንዲገቡ የፈቀደችላቸው ሀገራት እነማን ናቸው?ጀርመን በዓመት 400 ሺህ የውጭ ሀገራት ሰራተኞችን ትፈልጋለች ሰራተኛ ዕጥረቱን ለመፍታት በሚል የአውሮፓ ህብረት አባል ላልሆኑ ሀገራት አዲስ ስርዓት ዘርግታለችጀርመን የሰራተኛ ዕጥረቷን ለመፍታት በሚል ወደ ሀገሯ እንዲገቡ የፈቀደችላቸው ሀገራት እነማን ናቸው?የአውሮፓ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ጀርመን ከፍተኛ የሰራተኛ ዕጥረት እንደገጠማት አስታውቃለች፡፡ሀገሪቱ በተለይም ረጅም ዓመታትን ሊሰሩ ለሚችሉ የሰለጠኑ ወጣቶች ብዙ አማራጮችን ያቀረበች ሲሆን በተለይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና የጤና ሙያዎች የበለጠ ተፈላጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡ጀርመን እድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ፣ የሙያ ባለቤት እና ልምድ ያላቸው አመልካቾች ስራ እንዲፈልጉ በሚል ለአንድ ዓመት የሚቆይ ቪዛ እንደምትሰጥ አስታውቃለች፡፡እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ ከሆነ ጀርመን በዓመት 400 ሺህ የሰለጠኑ ሰራተኞችን የምትፈልግ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆኑ ሀገራት ስራ ፈላጊ ዜጎች በቀላሉ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ አመቺ የቪዛ ስርዓት መዘርጋቷንም አስታውቃለች፡፡
Al-Ain
More Stories
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑክ ቡድናቸው በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኤሊሴ ቤተመንግሥት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ተደራሽነትን በማረጋገጥ ረገድ ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ስራ አከናውናለች
ፕሬዚዳንት ፑቲን ጦርነቱን ማቆም ይፈልጋሉ፡- ፕሬዚዳንት ትራምፕ