March 30, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአፍሪካ ዋንጫ የተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ላይ ጭማሪ ተደረገ

ከቀጣዩ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ጀምሮ የተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ላይ ጭማሪ መደረጉን ካፍ አሳውቋል።

የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በትናንትናው ዕለት በግብፅ ካይሮ ባደረጉት ስብሰባ የተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ከ24 ወደ 28 ሀገራት እንዲያድግ መወሰኑ ተገልጿል።

የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ በሦስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ኬንያ፣ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የጣምራ አዘጋጅነት እንደሚካሄድ ይታወቃል።