March 19, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጥራት ያለዉ መረጃ ስረዓት በትምህርት ስረዓቱ ላይ ያለዉን ጉድለት ለመሙላት  ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ



‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት  ቢሮ የትምህርት አስተዳደር መረጃ ስረዓት  ዲጂታላይዘሽን ላይ ያተኮረ  የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነዉ።

‎በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃላፊ ደስታ ገነሜ(ዶ/ር) ጥራት ያለዉ መረጃ ስረዓት በትምህርት ስረዓቱ ላይ ያለዉን ጉድለት ለመሙላት  ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል ።

‎የትምህርት ጥራት አመላካች ከሆኑ ተግባራት መካከል አንዱ የትምህርት መረጃ ስረዓት መሆኑን ገልፀዉ በየደረጃው ያሉት አካላት  የትምህርት መረጃ በጥራት መሙላት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

‎በባለፉት  ግዜያት በማኑዋል ስሰራ የነበረዉ የመረጃ ስረዓት  ኦንላይን መደረጉን ተናግረው ይህም ጥራት ያለዉን የትምህርት መረጃ ለማደረጀት አይነተኛ ሚና እንደሚወጣ ገልፀዉ ለዚህም ርዕሰ መምህራን ድርሻቸዉ መወጣት  ይገባቸዋል ብለዋል።

‎የመምህራን ፣የተማርዎች ፣የትምህረት ቤቶች መረጃና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት መረጃ  በትክክል  ከመመዝገብ አንፃር የሚታዩ ክፍተቶች ማረም እንደሚገባ ገልጸዋል ።

‎በመድረኩ የቢሮዉ የትምህርት አመራር መረጃ ስረዓት ቡድን አቶ ታጠቅ ታደሰ በኩል ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።