March 16, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ በቀን 08/07/2018 ዓ/ም በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ማሻ፤ መጋቢት 8/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዞኑ ቴፒ ከተማ ላይ እንደሚያካሄድ የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ አቶ ጌታቸው ኬኒ ገልፀዋል።

በክልሉ በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ፀጥታን የማስጠበቅ ፣ የዝርፊያና የስርቆት ወንጀሎችን መከላከል እንዲሁም ከወሰን ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ የማድረግ ስራዎች ላይ ምክር ቤቱ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

ነገ በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ በ2018 ዓ.ም 6 ወራት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት ሪፓርት ቀርቦ ውይይቶች እንደሚደረጉ ዋና አፈጉባኤው በመግለጫቸው ጠቁመዋል ።

በጉባኤው ላይ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ፣ የሁሉም ብሔረሰብ ተወካዮች እና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ምክር ቤቱ አስታውቋል።